Главная
Загрузить
Каналы
F.A.Q.
Документация
Контакты
Ministry of Education Ethiopia
@ethio_moe
Подписчиков
28.8K
Подписчиков за неделю
100
Просмотров за неделю
30.9K
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel. For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Участники за неделю
Просмотры за неделю
Похожие каналы
TIKVAH-ETHIOPIA
Telegram: Contact @google_pay_stamp_go_india_offer
Telegram: Contact @Google_Pay_Go_India_Offer_Stampp
Vtube.Official
tutby_official
Тэги каналов
Telefon
лайфхаки
разам
Rek Boyicha Faqat Men
جيش الممثلات
حصريات
uydaqoling
all in one airdrop
فلسفة الحياة
پرایس اکشن
Подписчиков от
до
Просмотров от
до
Искать
Ministry of Education Ethiopia
"አረንጓዴ አሻራን በማኖር ለትውልድ የተሻለች አገር ማስረከብ ይገባል" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
.................................................
አረንጓዴ አሻራን በማኖር የአየር ንብረትን መጠበቅና ለትውልድ የተሻለች አገር ማስረከብ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ ።
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ''ኑ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ'' በሚል መሪቃል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አደኣ ወረዳ ሆረ ክሎሌ ቀበሌ በተደረገው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለጹት አረንጓዴ አሻራን በማኖር አገር መውደድን በተግባር መግለጽ ይገባል።
ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባም ፕሮፌሰር ብርሀኑ አሳስበዋል ።
የአደአ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አበበ በበኩላቸው የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ ሠራተኞቹ አረንጓዴ አሻራ በማኖራቸው አመስግነዋል።
በወረዳው ለአረንጓዴ አሻራ 23 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተው 96 በመቶ ያህሉ መተከላቸውን ኃላፊው ጨምረው አስረድተዋል።
በችግኝ ተከላው ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ( ዶ/ር) ፣የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አንዱአለም አድማሴ( ዶ/ር) ፣የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ ( ዶ/ር) እና የትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
Ministry of Education Ethiopia
በአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ መገንባት ተጀመረ
.............................................
በአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በደሴ ሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አዲስ የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች የወደፊቶቹ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች አቅጣጫ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የወደፊቱ አገር ተረካቢዎች የሚፈጠሩባቸው አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ በሁሉም ክልሎች ግንባታቸው እንደሚጀምርም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ተናግረዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው እንደ አዲስ በሚገነቡት ትምህርት ቤቶች ልጆቻችን በዕውቀት ፣ በክህሎትና በአመለካከት ተምረው ጊዜውን እንዲመጥኑ ማብቃት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ልማቱን ሊያፋጥንና ጠላትንም በንቃት መጠበቅ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የትምህርት ሚኒስቴር በክልሉ የወደሙ ትምህርት ቤቶች በተሻለ ጥራት መልሰው እንዲገነቡ በማድረጉ አመስግነዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ሚኒስትር፣ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ ፌደራልና ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአረንጓዴ የችግኝ ተከላ ስራም ተከናውኗል።
Ministry of Education Ethiopia
በአፋር ክልል በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
-------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ በጦርነቱ ከወደሙ ትምህርት ቤቶች መካከል የዳርሳጊታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ በአፋር ክልል ዳርሳ ጊታ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት የፈረሱ ትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው ከቀድሞ በተሻለ ደረጃ እንደሚገነቡ ተናግረዋል።
በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥም በአፋር ክልል በጦርነት የወደሙ 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚገነቡም ገልፀዋል።
አዲስ የሚገነቡት ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎች ፈልገው የሚማሩባቸው ፣ የቀለም ብቻ ሳይሆን የተግባርና የሙያ ትምህርት የሚሰጥባቸው የማህበረሰብ ዋና ማዕከላት ይሆናሉም ብለዋል።
ሞዴል ትምህርት ቤቶቹ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ጥራትና ደረጃቸውን ጠብቀው እንደሚገነቡም ተገልጿል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ ድጋፍ ያደረገውን በውጭ አገራት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድን አመስግነዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ በአግባቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።
በፕሮግራሙ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
Ministry of Education Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
መልካም በዓል!
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education Ethiopia
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
-------------------------------------
በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠመ የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል።
ተማሪዎችም ፈተናውን በጨዋነት እና እርጋታ እንደወሰዱም ተናግረዋል።
የክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችም ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ስራ አስፈጻሚዋ ገልፀዋል።
የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።
Ministry of Education Ethiopia
የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱን ለማሻሻል መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
-------------------------//---------------------------
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የፈተና አሰጣጥ ስርዓት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት በምክርቤት ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አሁን ያለውን የተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ስርዓት ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈተና ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ከቻይና መንግስት ጋር በመተባበር እየተሰራ እንዳለ ገልፀው ከቁጥሩ ጋር ተያይዞ ችግር ማጋጠሙን አብራርተዋል፡፡
የፈተና ስርዓቱ አውቶሜት እስከሚደረግ ድረስም የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱን ለማሻሻል እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ነገር ግን እንደ ሀገር “ፈተናን ለፖለቲካ አጀንዳ ማዋል ትክክል አይደለም” - ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርዓቱን ለማሻሻል ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል
1
2
3
4
5
6
7
8
9
...
15
»
3649838
Каналов
204424659
Сообщений