@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena Телеграм
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተማሪ ብንያም ቃል የተገባለትን አርቴፊሻል እጅ ተረከበ የሰው
ተማሪ ብንያም ቃል የተገባለትን አርቴፊሻል እጅ ተረከበ

የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰሎሞን አማረ ለተማሪ ብኒያም ኢሳይያስ ለመስጠት ቃል ገብተውለት የነበረውን ኦቶቦክ ማዮኤሌክትሪክ አርቴፊሻል እጅ አስረክበውታል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአጥንት ህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ ቢሮ በመገኘት አቶ ሰሎሞን አማረ ተወካይ ሙሉ ዕቃውን ለተማሪው አስረክበዋል።

ፕሮፌሰር ብሩክ በዚህ ወቅት የተማሪ ብኒያምን ጥንካሬ አድንቀው እርሳቸውና በዲፓርትመንታቸው በኩል በተለያየ መስክ ድጋፍ እንደሚደረግለት ተናግረዋል።

ተማሪ ብኒያም ከራሱ አልፎ ሌሎችንም ማገዝ እንዲችል አሁን ከሚደረግለት ድጋፍ ባሻገር በዘላቂነት በተቋሙ የአርቴፊሻል እጅ ማምረት ፕሮጀክት ውስጥ አባል የሚሆንበትን ዕድል እንደሚመቻቹለትም ፕሮፌሰር ብሩክ ገልጸዋል።

በጎ አድራጊው አቶ ሰለሞን አማረ ቀደም ሲል ለተማሪው ለመስጠት ቃል በገቡት መሰረት ነው የ25 ሺህ የእንግሊዝ ፓውንድ ዋጋ ያለው ዘመናዊ አርቴፊሻል እጅ ከነሙሉ መገጣጠሚያው ያስረከቡት።

በቅርብ ጊዜ ውስጥም አዲስ አበባ በመገኘት አርቴፊሻሉን ለተማሪው እንደሚገጥሙለትና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርጉለትም ቃል ገብተዋል።

ድጋፉን ያደረጉት በዘርፉ በበጎ አድራጎት ስራ የሚታወቁት አቶ ሰለሞን አማረ ይህ ዘመናዊ አርቴፊሻል እጅ ለቢንያም ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግለት ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው ተማሪ ብኒያም አንድ እጁ አካል ጉዳት ያለበት በመሆኑ በቅርቡ ትምህርቱን አትከታተልም በሚል ታግዶ እንደነበር ይታወሳል።

በቅርቡም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢኒያም ኢሳይያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ተማሪው በአሁኑ ወቅት ወደ ትምህርት ገበታው በመመለስ የአምስተኛ ዓመት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል።

ተማሪ ቢንያም እና አባቱ አቶ ኢሳይያስ በተደረገላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በጎ አድራጊውን አመስግነዋል።


@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
Hakim Doctors Ethio health tena
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena Телеграм
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል በዶ ር ሆነሊያት ኤፍሬም 1
የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ ምክንያቱ የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ

2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም ምክንያቱ በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን እንዲሁ ስለሚቀንስ

3) ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር

4) በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ፣ ቆስጣ እና አሣ የመሣሠሉትን

5) የጠዋት ፀሐይን መሞቅ ይህም ቫይታሚን ዲ እንዲመነጭና ካልሲየም በሰውነታችን እንዲወስድ ይረዳል

6) የሚወስዱትን የካፊን መጠን ይቀንሱ ምክንያቱም ካፊን ካልሲየም ከሰውነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ ነው

7) ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ይህም ሰውነትዎን ጥንካሬ እና መፍታታትን ስለሚሰጥ በቀላሉ ወድቀው ለስብራት እንዳይጋለጡ ይረዳል

8) ወደ ሐኪም በመሄድ ቅድመ ምርመራ ያድርጉ በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ ሴቶች ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!
ጤና ይስጥልኝ!

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
Hakim Doctors Ethio health tena
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena Телеграм
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena Телеграм
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአምባገንነታቸውና የማን አለብኝነታቸው ማሳያው ይሄ ሁሉ ሀኪም በዓንድ
የአምባገንነታቸውና የማን አለብኝነታቸው ማሳያው ይሄ ሁሉ ሀኪም በዓንድ ድምፅ እውነትን እየነገራቸው ስለጉዳዩ ምንም አይነት እርምትም ሆነ ማብራሪያ ሳይስጡ የሁሌም የተለመደ "ምንም አያመጡም" ባህሪያቸውን እያሳዩን ነው!

በሰንሰለት መልክ ተቆላልፈው በህክምና ትምህርት ቤት በዲፓርትመንት መሪነት ላይ ዘመናትን ያስቆጠሩ እና ተደላድለው የተቀመጡ አይነኬዎች ጊዜያቸው እንዳለቀ አለማወቃቸው እራሱ ይገርመኛል!

ወደዳችሁም ጠላችሁም አዲሱ ትውልድ አሮጌውን ጨቋኝ እና በዳይ የሲኒየርነት መገለጫ ባህሪ ከላዩላይ አንከባሎ ይጥላል!

በአመክንዮነት እና በሳይንስ እንጂ እንደባላባት ማንም ላይ የማይኩራራ ደግሞም እንደባሪያ ማንንም የማይፈራ ትውልድ የዘውጌ ወንበራችሁን ሊረከብ በበር ላይ ቆሟል!

ስለዚህ ፈላጭ ቆራጭ ሆናችሁ ለራሳችሁ ከገነባችሁት ከዚህች የህክምና ትምህርት ቤት ግዛት በራሳችሁ ጊዜ ወታችሁ ያዲሱን ትውልድ አስተሳሰብ ተቀላቀሉ! አለበለዚያ እመኑኝ ትንሽ ጊዜ ቢፈጅ ነው እንጂ ፍትህ እና አመክኗዊነት ፈላጊው ዘመንና ትውልድ ላይ እስከመታሰቢያም ቦታ አይኖራችሁም::

አዲስ አበባ ይንቨርስቲም የህዝብ እንጂ የግላችሁ ተቋም እስካልሆነ ድረስ ወዳችሁም ይሁን በፍርድ ቤት ተገዳችሁ ዶ/ር ታዝባቸው ፍትህን ያገኛል!

ማንም ከህዝብና ከፍትህ በላይ እስካልሆነ ድረስ ደግሞ በመልካም አስተዳደር ጉለት ፍትህን በመበደል ይህ ሁሉ ሀኪም ፍትህን እየለመናችሁ እንኳን መፍትሄ አምጪ አካል ለመሆን ባለመፈለጋችሁ ዋጋ ትከፍላላችሁ! ተገምግማችሁ በህዝብ አደራ የተቀመጣችሁበትን ቦታ በታማኝነት ስላላገለገላችሁ ለቦታው የሚመጥን ሰው ተቀምጦ ይህን ውሳኔ ያስተላለፋችሁ መነሳታችሁ አይቀሬ ነው!

የተቀመጣችሁበት ቦታ የቀጣይ ትውልድ ሀኪሞችን በአመክንዮ ፣ በፍትህ እና እኩልነት እንድታበቁበት እንጂ በአንባገነንነትና ፍርደ ገምድልነት ትውልዱን እንድታስለቅሱ አይደለም::

በራስ መተማመን ያለው ተማሪ ስታዩ እናስተንፍሰው (Let us deflate him) እያላችሁ የስንቱን ሩጫ እና ራዕይ አስጨናገፋችሁ!

አሁን ግን ይህን ሁላ ግፍ በቃችሁ የሚል የሀኪሞች ትውልድ መጥቷል! የዘመኑን አስተሳሰብ የማይመጥን አመራርነት ተቀባይነት የለውም::

ፍትህ ለዶ/ር ታዝባቸው እንባ!
ፍትህ ይሄ ዱላ ለሚያርፍባቸው የቀጣይ ትውልድ የህክምና ተማሪዎች
#JusticeforDrTazebachew

Dr. Abraham Tariku

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena

3649838

Каналов

204424659

Сообщений