ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው
ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው
.
የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
.
በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3wwmEqo
በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትላልቅ ሆቴል ባለቤቶች
በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትላልቅ ሆቴል ባለቤቶች መቋቋሚያ ብድር ባለማግኘታቸው ሆቴላቸውን ለመሸጥ እንቅስቃሴ አያደረጉ ነው።
.
በኮቪድ-19 አስከፊ ተጽእኖ የሆቴል ኢንዱስትሪውን ለመታደግ መንግሥት ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ብድር ለመስጠት በወሰነው መሠረት በአንድ አመት የሚመለስ 3.3 ቢሊዮን ብር በንግድ ባንኮች አማካኝነት አበድሮ ነበር። ሆኖም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሁኔታዎች ባለመሻሻላቸው የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች የንግድ ዘርፍ ማኅበር የንግድ ባንኮች የብድር መክፈያ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ ለብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ውሳኔ እንዲሰጥ ቢጠይቅም፣ ጥያቄ በአየር ላይ የቀረ ይመስላል።
.
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አስቴር ሰለሞን እንደገለፁት የመክፈያ ጊዜው 3 ወር ብቻ የቀረው ሲሆን ብዙ የሆቴሎች ባለቤቶች በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ሆቴላቸውን ለመሸጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። በጎን በኩል ደግሞ ባንኮች ብድራቸውን ያልከፈሉ ሆቴሎችን በጨረታ የመሸጥ ሂደት እየጀመሩ ነው።
.
መንግሥት የወሰደው እርምጃ ዘርፉን በወቅቱ የታደገው ቢሆንም አሁን ላይ ግን የብድር ጊዜ ካልተራዘመ በስተቀር በሆቴሉ ላይ ያለው ሥጋት አሁንም ሊፈታ አይችልም ሲሉ ወ/ሮ አስቴር አስረድተዋል አክለውም አበዳሪዎች የሆቴሎችን ችግር ተረድተው የመክፈያ ጊዜውን ማራዘም ቢፈልጉም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ውጭ ማድረግ አይችሉም በማለት አስረድተዋል።
https://www.capitalethiopia.com/.../loans-weigh-hefty.../
በቆቦ ከተማ ለህወሀት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን
በቆቦ ከተማ ለህወሀት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ
.
በቆቦ ከተማ በጋሪ ብረቶች ውስጥ ተደብቆ ለህወሃት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቆቦ ከተማ ህዝብ፣ በከተማው ፓሊስና በሕዝባዊ ሚኒሻ ሠራዊቱ አማካኝነት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።
.
የቆቦ ከተማ አስተዳደር ሠላም እና ፀጥታ ሀላፊ ሀምሳ አለቃ አበበ ደርሶ እንደተናገሩት፤ "ብዙው ነገር ሲደረስበት ባልተነቃ መልኩ ለጁንታው እናደርሳለን ያሉት የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም ወገናቸውን አሳልፎ እንዲሰጡ ቢደረግም በኹሉም የፀጥታ ሃይላችን አማካኝነት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።"
.
የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ፅ /ቤት ሀላፊ ኮማንደር ታደሰ ተሰሜ በበኩላቸው፤ ጋሪው የተሰራው ሙሉ በሙሉ ውስጡ ክፍት በመሆኑ፤ ሥም የተፃፈበት ብር በእያንዳንዱ ብረት በማድረጋቸው ላለመያዝ የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም የቆቦ ከተማ ህዝብም ይሁን የፀጥታ አካሉ በመግባባቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለዋል።
.
ኮማንደር ታደሰ እና ሀምሳ አለቃ አበበ በጋራ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ኹላችንም በጋራ ከሰራን ከዚህ የበለጠ ችግር ቢገጥመንም በጋራ የማንወጣው አስከፊ ችግር ስለማይኖር አገር የማዳን ሥራችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልፀው፤ የቆቦ ከተማ ህዝብ ካጠገባችን በመሆኑ ኹሌም ኩራት ይሰማናል ማለታቸውን ከቆቦ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
አዲስ ማለዳ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለማችን ተፅእኖ ፈጣሪ 100
➡️ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለማችን ተፅእኖ ፈጣሪ 100 ሰዎች አንዱ ሆነው ተመረጡ!
➡️የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር የነበሩት ከእስር ተለቀቁ!
➡️ፈንጣጣ መሰሉ ቫይረስ ወደኢትዮጵያ እንዳይገባ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ!
➡️የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ በሽርክና ሊሰሩ ነው!
➡️አሜሪካ ለኢትዮጵያ ስኳር ልትሸጥ ነው!

https://youtu.be/qUeNI7W2r7A
የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ
የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለፀ።

የተቋሙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለአል ዓይን ኒውስ እንደገለፁት ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ ነው፡፡

እንደማንኛውም አገር በኢትዮጵያም የቫይረሱ ስርጭት ስጋት አለን ብለዋል።

በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ነው ማለታቸውን የአልዐይን ዘገባ ያሳያል።
በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመርና ቆጣሪ
በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመርና ቆጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
*
በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ የተዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመርና ቆጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 5 አገልግሎት መስጫ ማዕከል እዳስታወቀው ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ መሰረት ከአካባቢው ፖሊስ ጋር በመተባበር በተደረገ አሰሳ ስምንት ምሰሶ ተተክሎ፣ መስመር ተዘርግቶ 12 ቆጣሪ በህገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው አገልግሎት ሲሰጡ ተገኝቷል፡፡
ልዩ ስሙ ወጂ መድሐኔአለም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዘርግተው የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ሲጠቀሙ እንደተገኙ ማዕከሉ አስታውቋል፡፡
በከተማው በህገ-ወጥ መንገድ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የማፍረስና የተገጠሙ ቆጣሪዎችን የማንሳት እርምጃ መወሰዱም ተመልክቷል፡፡
የተገጠሙ ቆጣሪዎች ተቋሙ የማያውቃቸው እና የተቋሙ አርማ የሌላቸው መሆናቸው በእርምጃው ወቅት መረጋገጡንም ጠቁመዋል፡፡
ደንበኞች አዲስ ቆጣሪ ማስገባት ሲፈልጉ ተቋሙ ያስቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት እና ህጋዊ መንገድን በተከተለ መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡም መሰል እኩይ ተግባር ሲመለከት ለተቋሙና ለህግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥና ህገ ወጥ ተግባርን በጋራ መከላከል እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ግንቦት 12 2014 ኢትዮጵያ በገጠማት የውጪ ምንዛሪ እጥረት
ግንቦት 12፣ 2014

ኢትዮጵያ በገጠማት የውጪ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የተወሰኑ የፍጆታ እቃዎችን (በፍራንኮቫሉታ) ወደ ሀገር እንዲያስገቡ የውጪ ምንዛሪ ለሚያገኙ ዜጎች በቅርቡ እድል መሰጠቷ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ግለሰቦች የውጪ ምንዛሪን በራሳቸው ፈልገው የፍጆታ እቃዎችን እንዲያስገቡ ከሰጠው ፈቃድ በተጨማሪ በመንግስት የልማት ድርጅቶች በኩል ተፈፃሚ የሚደረግ የዱቤ ግብይት ሥራ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡

ለመሆኑ የዱቤ ግብይት ወይም ዲፈርድ ሌተር ኦፍ ክሬዲት አሰራሩ እንዴት ይሆን?

ትዕግስት ዘሪሁን

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የዱቤ_ግብይት

https://bit.ly/3LETVnj

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz

3649838

Каналов

177451917

Сообщений