ምክር ለወጣት ሴቶች ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል
👉👉#ምክር_ለወጣት_ሴቶች👈👈

ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡
የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡
አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

👉አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ

👉ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!

👉ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"

ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡

የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር #በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡

በመጀመሪያ መንግስታችሁን (#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)

ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡

#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት

ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ እበረታቷቸው

@mahibretsadkan ይቀላቀሉን።
እንኳን ለቅዱሳኑ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ቂርቆስ ወኢየሉጣ በጥላን
††† እንኳን ለቅዱሳኑ ገብርኤል ሊቀ መላእክት: ቂርቆስ ወኢየሉጣ: በጥላን ጠቢብ እና ሰማዕታተ እስና ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ: ወቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር::

ከሮም ግዛት በአንዱ ከቅዱስ ልጇ ጋር የምትኖረው ቅድስት ኢየሉጣ የስደቱ ዘመን ሲመጣ እርሷም እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ተሰደደች:: እስክንድሮስ የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ግን ያለችበት ድረስ ተከትሎ እንድትያዝና እንድትቀርብ አደረገ::

ወዲያውም "ስምሽ ማን ይባላል?" ቢላት "ክርስቲያን እባላለሁ" አለችው:: ንጉሡ ተቆጣ:: "መዋቲ ስሜን ከፈለክ ኢየሉጣ ይባላል" አለችው:: ንጉሡ መልሶ "አሁን ለጣዖት ካልሠዋሽ ሲጀመር ስቃይ: ቀጥሎም ሞት ይጠብቅሻል" ቢላት ቅድስቲቱ መልሳ "በከተማ ውስጥ የሦስት ዓመት ሕፃን አለና እርሱን አምጣው:: ማንን ማምለክ እንዳለብን ይነግረናል" አለችው::

አስፈልጐ ቅዱስ ቂርቆስን አስመጣው:: "ስምህ ማን ይባላል?" አለ ንጉሡ:: "ከማይደፈርስ ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ ጥሩ ምንጭ ስሜ ክርስቲያን ይባላል:: መዋቲ ስሜን ከፈለግህ ግን ቂርቆስ ይባላል" አለው::

ንጉሡ ሊያታልለው "ደስ የተሰኘህ ሕፃን" ቢለው ቅዱሱ ሕፃን "ትክክል ተናገርክ: ለእኔ በሰማያት ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን እውነተኛው አምላክ ይፈርድብሃል" አለው:: በሦስት ዓመት ሕፃን አንደበት ዘለፋ የገጠመው ከሃዲ ተቆጣ::
እናትና ልጅን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃያቸው::

ሰውነታቸውን ቸነከረ: አካላቸውን ቆራረጠ: ዓይናቸውን አወጣ:: ሌላም ሊናገሩት የሚጨንቅ ስቃይን አሰቃያቸው:: በዚህች ቀን ግን ትልቅ ድስት አሰርቶ ባሩድ: አረር: ስብና የመሳሰሉትን ጨምረውበት በእሳት አፈሉት::

የእሳቱ ወላፈን አካባቢውን በላው:: በድስቱ ውስጥ ያለው ነገር እየፈላ ሲገላበጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ይጮህ ነበር:: የስድስት ሰዓት የእግር መንገድ ድረስም ተሰምቷል:: ቅድስት ኢየሉጣ ይሔኔ ነበር ልቧ ድንግጥ ያለው:: ሕፃኑ ቂርቆስ የእናቱን ፍርሃት ሲመለከት ጸለየ::

"ፈጣሪዬ! ፍሬው ያለ ግንዱ አይቆምምና እኔን እንዳጸናሕ እናቴንም አጽናት" ሲል ለመነ::
"እግዚኦ ትፈቅድኑ ለፍሬሁ ተአልዶ:
እንዘ በእሳት ታውኢ ጉንዶ" እንዲል::
በዚያች ሰዓት ቅድስት ኢየሉጣ ዓይኖቿ ተከፍተው ሰማያዊ ክብርን ተመለከቱና ልቧ ወደ ድፍረቱ ተመለሰ::

ልጇንም "አንተ አባቴ ነህ: አንተን የተሸከመች ማኅጸኔ የተባረከች ናት" አለችው:: ከዚያም ሁለቱንም ወደ ፈላው ድስት ውስጥ ቢጨምሯቸው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደላቸው:: በበትረ መስቀሉ ባርኮ የፈላውን አቀዘቀዘው:: የነደደውን ውኃ አደረገው:: ቅዱሳኑ ቂርቆስና ኢየሉጣ ከብዙ መከራ በኋላ በሰማዕትነት አልፈዋል::

††† ቅዱስ በጥላን ጠቢብ †††

††† ቅዱሱ ከአሕዛብ ወላጆቹ ተወልዶ: ያደገውም በጣዖት አምልኮ ነው:: በሙያው እጅግ የተመሠከረለት ሐኪም ነበር:: የሃገሩ ሰዎች "ጠቢብ" እያሉም ይጠሩታል:: በጥላን ምንም ጣዖት አምላኪ ቢሆን በተፈጥሮው ተመራማሪና ቅን ነበር::

አንድ ካህንም በጐረቤቱ ነበርና ዘወትር ስለ ሃይማኖት ይከራከሩ ነበር:: ካህኑ ሌሊት ሌሊት ስለ በጥላን ተግቶ ይጸልይ ነበርና ተሳክቶለት አሳመነው::

አንድ ቀን በጥላን መንገድ ሲሔድ እባብ ሰው ነድፎ ለሞት ደርሶ አየውና ጸሎት አድርሶ ስመ ክርስቶስን ቢጠራ የተነደፈው ድኖ እባቡ ሞተ::

በዚህ ተዓምር ደስ ብሎት ወደ ካህኑ ሒዶ ተጠመቀ:: ከዚያም ጾም ጸሎትን ጀመረ:: በየቦታው እየዞረ ሕሙማንን እንደ ቀድሞው በመድኃኒት ሳይሆን በጸሎት ያድናቸው ነበር:: ስላዳናቸውም በርካቶቹ ወደ ክርስትና መጡ::

የአካባቢው ሰው: ወላጆቹን ጨምሮ ክርስቲያኖች ሆኑ:: በመጨረሻም ቅዱስ በጥላን: ቤተሰቦቹ: ካህኑና ከደዌ የዳኑት ወገኖቹ በአካባቢው ጣዖት አምላኪ ንጉሥ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ሰብከው በሰማዕትነት ዐርፈዋል::

††† ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና †††

††† እስና ማለት ግብጽ ውስጥ የምትገኝ የቀድሞ አውራጃ ናት:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በከተማዋ በርካታ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የእንዴናው መኮንን መጥቶ "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: ሕዝቡ በአንድ ድምጽ መለሱ:- "ይሕማ ፈጽሞ ሊደረግ አይችልም::" መኮንኑ ተቆጥቶ "ሁሉንም ግደሉ" አለ::

ወታደሮቹ ሰው አልመረጡም:: ከታዘለ ሕፃን አልጋ ላይ እስካለ ሽማግሌ: ከጤነኛ እስከ ሕመምተኛ: ሁሉንም ጨፈጨፏቸው:: ከተማዋ በደም ተነከረች:: ከከተማዋ ክርስቲያኖች ወሬ ለመንገር አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም:: ሁሉም ስለ ክርስትና ደማቸውን አፈሰሱ::

††† ጌታችን ስለ ሰማዕታቱ ብሎ: ደማቸውንም አስቦ በሃይማኖታችን ያጽናን:: ከመከራም ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያድለን::

††† ሐምሌ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ኢየሉጣ
3.ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ሰማዕት እና ማኅበሩ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
3.አቡነ ስነ ኢየሱስ
4.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ መራቆት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቆጠርን::' ተብሎ እንደተጻፈው ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፯)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@mahibretsadkan
እሰከመጨረሻው አንብቡት share mahibretsadkan አንድ ሰው መኪናውን ለረጅም
#እሰከመጨረሻው_አንብቡት share
@mahibretsadkan
አንድ ሰው መኪናውን ለረጅም ሰዓት ሲያሽከረክር ቆይቶ ከአንድ ጥንታዊ ገዳም ደጃፍ ሲደርስ ብልሽት ያጋጥመውና ይቆማል በዚህ ጊዜ ወደ ገዳሙ ደጅ በማምራት በሩን ማንኳኳት ጀመረ በሩ ተከፍቶለት ሲያበቃም " እባክዎን መኪናዬ በድንገት ተበላሸች" ምናልባት ከእናንተ ዘንድ ይህን ሌሊት ማሣለፍ እችል እንደሆነ ለመጠየቅ ነበር በማለት ለመነኩሴው ጥያቄ አቀረበ መነኩሴውም የሰውዬውን ጥያቄ በደስታ ተቀብለው ማደሪያውን አዘጋጁለት ፣ ራት ጋበዙት ፣ እንዲሁም መኪናውን ጠገኑለት ከመሸ በኋላ ሰውዬው መኝታው ላይ ጋደም እንዳለ አንድ እንግዳ እና የሚደንቅ ድምፅ ሰማ በሰማው ድምፅ እጅግ ተደንቆ ሌሊቱን አሳለፈና በማለዳ ወደ መነኩሴው ዘንድ በመሄድ ስለሰማው ድምፅ ጠየቃቸው መነኩሴውም ወዳጄ አንተ መነኩሴ ባለመሆንህ ስለ ድምፁ ልነግርህ አይቻለኝም ስለ ድምፁ ለማወቅ በጣም ፍላጎት ስላደረበት ይህንን ለማወቅ መሆን ከተገባ እንዴት መነኩሴ እንደምሆን ይንገሩኝ ይላቸዋል መነኩሴውም በምድር ዙሪያ ልትዞር እና ምን ያህል ሳር እንደበቀለ በላይዋ የተዘራው አሸዋ ቁጥርም ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅና ለመናገር ከቻልክ በዚህ ገዳም መነኩሴ አድርገን እንቀበልሃለን የድምፁንም ሚስጥር ያን ጊዜ ታውቃለህ አሉት ሰውዬው ስለ ድምፁ ሚስጥር ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት አድሮበት ስለ ነበር የተጠየቀውን ለመፈፀም በቁርጠኝነት ጉዞውን ጀመረና ለአርባ አምስት አመታት የምድርን ሳርና አሸዋ ሲቆጥር ኖሮ ተመለሰ ። @mahibretsadkan
እነሆ እንደተጠየቁት በምድር ዙሪያ የበቀለውን ሳር የተዘራውን አሽዋ ስቆጥር ኖሬ ተመለስኩ 134566778876 ሳር የበቀለ ሲሆን 3456787654445አሽዋ ደግሞ በምድሪቱ ላይ ይገኛል በማለት ተናገረ
መነኩሴው በአድናቆት እንኳን ደስ አለህ ከዚህ በኋላ መነኩሴ ሆነሃል አሁን ወደ ድምፁ ስፍራ እወስድሃለሁ በማለት እየመሩት ከምድር ስር ወደ ተገነባ ቤት ወሰዱት ።
በዚያም አንድ የእንጨት በር እያሳዩት ድምፁን ከዚያ በር ጀርባ ታገኘዋለህ አሉት ሰውዬው ወደ በሩ ሂዶ ለመክፈት ቢሞክር ተቆልፎ ነበር እባክዎን አይቀልዱብኝ በሩ ተቆልፏል አላቸው መነኩሴውም የበሩን ቁልፍ አቀበሉትና ሰውዬው ከፍቶ ወደ ውስጥ ዘለቀ ነገር ግን ከውስጥ ደግሞ ሌላ ከድንጋይ የተቀረፀ በር አጋጠመው አሁንም የድንጋዩን በር መክፈቻ እንዲሰጡትና የጓጓለትን የድምፁን ሚስጥር ለማወቅ እንዲችል ጠየቃቸው የድንጋዩን በር መክፈቻ መነኩሴው ሰጡትና አሁንም ከፍቶ ወደ ሌላው ክፍል መግባት ቢችልም ሌላ እጅግ የከበረና የተወደደ ቀይ አንፀባራቂ እንቁ የተሠራ በር ደግሞ አጋጠመው አሁንም መነኩሴው የዚህን ቁልፍ እያቀበሉት ይህን በር ስታልፍ በእርግጠኝነት የዚያን ድምፅ ምንነት ታያለህ ታውቃለህም አሉት
በዚህ ጊዜ ሰውዬው ታላቅ ደስታና እፎይታ ተሰማው በሩን ከፍቶ ወደዚያ የአስደናቂ ድምፅ ምንጭ ወደሆነው ክፍል ገባ ።
ውድ አንባቢ! ስለዚህ ድምፅ ምንነትና ሚስጥር ብነግርህ ደስ ይለኝ ነበር ፤ ነገር ግን መነኩሴ አይደለህም ።

ሼር ከወደዳችሁት
👇👇👇👇👇👇
@mahibretsadkan
@mahibretsadkan
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለነቢዩ #ቅዱስ_ዮናስ እና ለእናታችን #ቅድስት_አውፎምያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ ቅዱስ ዮናስ ነቢይ ✞✞✞

=>በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ዮናስ ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት እንደ ነበረ ይታመናል:: #ሊቃውንት እንዳስተማሩን ደግሞ እናቱ #ቅዱስ_ኤልያስን የመገበችው የሰራፕታዋ መበለት ናት:: ቅዱስ ዮናስ ገና ሕጻን ሳለ በእሥራኤል ምድር ዝናብ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ተከልክሎ ነበር::

+ይሕንንም ያደረገው ደጉ ነቢይ ኤልያስ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀንቶ ነው:: በወቅቱ ኤልያስ በሰራፕታ ሳለ ሕጻኑ ዮናስ ታሞ ሞተ:: ልጇ የሞተባት መበለትም ኤልያስን ለመነችው:: ኤልያስም ወደ ፈጣሪው ማልዶ ሕጻኑን ዮናስን ከሞት አስነስቶታል:: ትንሽ ከፍ ባለ ጊዜም ከጉዋደኞቹ (ከነቢያቱ) #አብድዩና #ኤልሳዕ ጋር ሆነው ታላቁን ነቢይ ኤልያስን ተከትለውታል::

+ኤልያስ ካረገ በሁዋላ ሁሉም በየተሰጣቸው አገልግሎት ተሠማርተዋል:: ቅዱስ ዮናስን #እግዚአብሔር "ወደ ነነዌ ሒደሕ ንስሃን ስበክ" አለው:: ዮናስ ግን የፈጣሪውን መሐሪነት ጠንቅቆ ያውቃልና አልሔድም አለ:: (ተመልከቱ የየዋሕነት ብዛት)

+እግዚአብሔር እየደጋገመ እንዲሔድ ሲነግረው ነቢዩ "እንዲሕ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል" ብሎ ሊኮበልል ወጣ:: ነገር ግን አልቀናውም:: በእርሱ ምክንያት ማዕበል ተነሳ:: ሕዝቡም ሊያልቁ ሆነ:: ከእንቅልፉ የነቃው ዮናስ ከመርከቡ ላሉት አሕዛብ አምልኮተ እግዚአብሔርን ሰብኮላቸው: በእርሱ ጠያቂነት ሐምሌ 15 ቀን ወደ ባሕር ጥለውታል::

+አሣ አንበሪም ተቀብሎታል:: በግዙፉ አሣ ውስጥም ያለ እንቅልፍ በጾም: በጸሎትና በምስጋና 3 ለቀን ቆይቷል::
ሙስና ሳያገኘውም በዚህች ቀን አሣ አንበሪው #ነነዌ ዳር ላይ ተፍቶታል:: ቅዱስ ዮናስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዓባይ ሃገር" /እስከ ሦስት ቀን ድረስ ነነዌ ትገለበጣለች (ዮናስ 3:4)/ ብሎ አሰምቶ ሰበከ::

+የነነዌ ሰዎችም በስብከተ ዮናስ አምነው: ንስሃም ገብተው ድነዋል:: በዚህም ጌታችን በወንጌል ላይ አመስግኗቸዋል:: ቅዱስ ዮናስ መኮብለሉ #በሐዲስ_ኪዳን ለሚደረገው ምስጢረ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነውና ይደነቃል:: (ማቴ. 12:38) ነቢዩ ግን በተረፈ ሕይወቱ ሕዝቡን ሲያስተምር: ፈጣሪውን ሲያገለግል ኑሮ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::

+"+ ቅድስት አውፎምያ ሰማዕት +"+

=>እናታችን #ቅድስት_አውፎምያ (ስሟ አፎምያ አይደለም:: በስሕተት "ው" መካከል ላይ የገባች እንዳይመስልዎ:: እስመ ከመዝ ስማ-ስሟ እንዲሁ ነው የሚጠራው) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ወጣት ክርስቲያኖች አንዷ ናት:: ገና ከልጅነቷ ልቧ በፍቅረ ክርስቶስ የተነደፈ ነበር::

+በዚህም ምክንያት ራሷን በጾምና በጸሎት ወስና ትኖር ነበር:: እድሜዋ ገና በአሥራዎቹ ቢሆንም በመንኖ ጥሪት መኖር ምርጫዋ ነበር:: ሊቃውንት አበው ከሰማዕትነቷ ደርበው "ጻድቅት አውፎምያ" እያሉም ይጠሯታል::

+አንድ ቀን ግን መንገድ ወጥታ ነበርና ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ ተመለከተች:: ምንም ጥፋት ሳይገኝባቸው ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ይሙት በቃ ተፈርዶባቸው ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር:: አሕዛብ ግብራቸው የአውሬ ነውና ርሕራሔ የላቸውም:: ሰማዕታቱ ደማቸው በየመንገዱ እየፈሰሰ ጥቁር ሰንሰለት በአንገታቸው: በእጃቸውና በእግራቸው ላይ አድርገው ይጐትቷቸው ነበር::

+ቅድስት አውፎምያ የተደረገውን ሁሉ ተመልክታ አምርራ አለቀሰች:: ፈጠን ብላም ወደ መኮንኑ ቀርባ ገሰጸችው::
"አንተ አእምሮ የጎደለህ! እንዴት ክርስቲያኖችን እንዲህ ታሰቃያለህ? አምላካቸው #ጌታ_ክርስቶስ ታጋሽ ባይሆን ኑሮ በቅጽበት ከገጸ ምድር ባጠፋህ ነበር" አለችው::

+በድፍረቷ የተገረመው መኮንኑ "አንቺስ ማንን ታመልኪያለሽ?" ሲል ጠየቃት:: እርሷም "ሰማይና ምድርን የፈጠረውን: ስለ እኛ ሲል በቀራንዮ አንባ የተሠዋውን #ኢየሱስ ክርስቶስን አመልካለሁ" ስትል መለሰችለት:: በዚያች ሰዓት የመኮንኑ ቁጣ በቅድስቷ ላይ ነደደ::

+ነገር ግን ቁጣውን ከቁም ነገር አልቆጠረችውምና እንዲያሰቃዩዋት አዘዘ:: ወታደሮቹ ሥጋዋን በብዙ አሰቃዩ:: ብላቴናዋ አውፎምያ ግን ጽንዕት ናትና አልቻሏትም:: በመጨረሻ በእሳት ተቃጥላ ትሞት ዘንድ ተፈረደባት::

+እሳቱ ከመሬት ከፍ ባለ ጊዜ ወደ ውስጥ ወረወሯት:: በእሳቱ መካከል ቁማ ለረዥም ጊዜ ጸለየች:: ከዚያም ነፍሷን አሳልፋ ሰጠች:: ምዕመናን በክብር ገንዘው ቀብረዋታል::

=>አምላካችን ከነቢዩና ከሰማዕቷ ወዳጆቹ በረከት ይክፈለን::

=>ሐምሌ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ (ከአሣ አንበሪ ሆድ የወጣበት)
2.ቅድስት አውፎምያ (ጻድቅትና ሰማዕት)
3.ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕት (ታላቁ)
4.ቅዱስ ዘካርያስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

=>+"+ በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና:- 'መምሕር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን' አሉት:: እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው:- 'ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ:: +"+ (ማቴ. 12:38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/ortodoxmezmur21
ናህዲ ማሕሙድ ሙትዋሊ ክፍል 9 አንድ ትልቅ ፒራሚድ
ናህዲ ማሕሙድ ሙትዋሊ

ክፍል 9

· አንድ ትልቅ ፒራሚድ አናቴ ላይ ነበር የመሰለኝ።

ክርስትና በአንድ አምላክ ማመንን ያስተምራል የሚለው ለእኔ እንግዳ ነገር

ነው ይህ ጉዳይ እኔ ሰለ ክርስትና ከማስበው ፈጹሞ የተለየ ነው

ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ እና ጨካኝ የሆንኩት ባለማወቄ መሆኑ ገባኝ።

ምንም እንኳን በውስጤ ፀፀት እና ሐፍረት ቢሰማኝም ከእርሷ ግን ብዙ ነገር

ለመስማት ጓጓሁ። በክርስቲያኖች ላይ የፈጸምኩት ሁሉ ትዘ አለኝ። ምን ዓይነት

አሰቃቂ ወንጀል ነው በእነርሱ ላይ ስፈጽም የኖርኩት? ሰለ እነርሱ የበለጠ

ለማወቅ ጓጓሁና <<እስቲ ሰለ ክርስትና ነገርኝ >> ሰል ጠየቅኳት።


የናህዲ ማሕሙድ ሙትዋሊ

ክፍል 10

ስለ ክርስትና መናገር ስትጀምር የዕጣን መዓዛ ክፍላችንን ዐወደው።

የሚገርም እኮ። እንዲህ ያለ መዓዛ ከዚያ በፊት ሸትቶኝ አያውቅም።

ዐቅሌን የሳትኩ መሰለኝ። ለመሆኑ በሕልሜ ነው ወይስ በእውኔ ይህ ሁሉ የሚሆነው? ስል ራሴን ጠየቅኩ።

ሃሳቤን እንደ ምንም አሰባሰብኩትና ገለጻዋን በጥሞና መከታተል ጀመርኩ።

<<ድንግል ማርያም ከእናንት ከአባትዋ ተለይታ አሥራ ሁለት ዓመት እስኪሆናት ድረሰ በቤተ መቅደስ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት አደገች።

ከዚያም በትውፊቱ መሠረት ይጠብቃት ዘንድ ለአንድ አረጋዊ አደራ ተሰጠች፣ ነገር

ግን በሁለቱ መካከል ምንም ዓይነት ግንኘነት ሳይኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ወለደች>>


በመሐል አቋረጥኳትና <<ልክ ነሺ ይህማ በቁርዐንም ተገልጧልኮ >> አልኳት።

ከዚያ በኋላ ውይይቱን መቀጠል አልቻልኩም።

የድካም እና የማድረቅ ሰሜት ተሰማኝ። ውይይታችንም እዚያ ላይ ተገታ።

እርሷም በውስጤ የፈጠረችውን ነገር ሳትረዳ ቢሮውን ለቅቃ ወጣች።

እንደ እውነቱ ከሆነ ላጠፋው የማይቻለኝ እሳት ለኩሳብኝ ነበር የሄደችው።

ይቀጥላል

💚 @ortodoxmezmur21
💛 @ortodoxmezmur21
❤️ @ortodoxmezmur21
እንኳን ለቅዱስ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ዓመታዊ የዕረፍት
††† እንኳን ለቅዱስ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ) †††

††† ቅዱሱ "ወንጌሉ ዘወርቅ" እየተባለ የሚጠራው ከሌሎች ዮሐንስ ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው: ከእጁ የማይለየውና አቅፎት የሚተኛ በወርቅ የተለበጠ ወንጌል ስለ ነበረው ነው::

የቅዱስ ዮሐንስ ታሪኩ ከመርዓዊ (ሙሽራው) ገብረ ክርስቶስ እና ከቅዱስ ሙሴ ሮማዊ ጋር ተመሳሳይነት አለው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በሮም ግዛት ሥር የሚኖሩ አጥራብዮስና ብዱራ የሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ:: እግዚአብሔር በቀደሰው ትዳር የሚኖሩና ነዳያንን የሚዘከሩ ነበሩና ይህንን ቅዱስ ወለዱ:: ስሙን ዮሐንስ ብለው: እንደሚገባም አሳድገው: ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን እንዲረዳ ለመምህር ሰጡት:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመምህሩ ዘንድ ቁጭ ብሎ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ተማረ::

ለወላጆቹ ቅንና ታዛዥ ነበርና አባቱ "ልጄ! የምትፈልገውን ጠይቀኝ:: ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?" አለው:: ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድሮ እኛን የሚያምረን ሁሉ አላሰኘውም:: አባቱን "ቅዱስ ወንጌልን ግዛልኝ: በወርቅም አስለብጠው" አለው:: አባትም የተባለውን ፈጸመ::

ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ከዚህ ዓለም ተለይቶ እስካረፈባት ቀን ድረስ ቅዱስ ዮሐንስና የወርቅ ወንጌሉ ተለያይተው አያውቁም:: ሁሌም ያለመታከት ያነበዋል:: ሲቀመጥም ሲነሳም: ሲሔድም ሲተኛም አብሮት ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ወጣት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይድሩት ዘንድ ተዘጋጁ:: ልብሰ መርዐም (የሙሽራ ልብስ) አዘጋጁ:: በዚያው ሰሞን ግን አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤታቸው መጥቶ ያድራል:: በዚያች ሌሊት መነኮሱ በጨዋታ መካከል ስለ ቅዱሳን መነኮሳት ተጋድሎና ክብር ነገረው:: የሰማው ነገር ልቡናውን የማረከው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚያች ቀን ጀምሮ ወደ ፈጣሪው ይለምን ነበር::

አንድ ቀን ግን ያ መነኮስ በድጋሚ መጥቶ አደረ:: ቅዱስ ዮሐንስ መነኮሱን ወደ ገዳም እንዲወስደው ቢጠይቀው "አይሆንም: አባትህ ያዝንብኛል" አለው:: ቅዱሱ ግን "በእግዚአብሔር ስም አማጽኜሃለሁ" ስላለው ሁለቱም በሌሊት ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::

አበ ምኔቱ "ልጄ! የበርሃውን መከራ አትችለውም: ይቅርብህ" ቢለውም "አባቴ! አይድከሙ:: ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር አይለየኝም::'' ስላላቸው እንደሚገባ ፈትነው አመንኩሰውታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመነኮሰ በኋላ በጾም: በጸሎት: በስግደትና በትሕርምት ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን አስደነቀ::

ለሥጋው ቦታ አልሰጣትምና በወጣትነቱ አካሉ ረገፈ:: ቆዳውና አካሉም ተገናኘ:: ሥጋውን አድርቆ ነፍሱን አለመለማት:: በእንዲሕ ያለ ሕይወት ለሰባት ዓመታት ከተጋደለ በኋላ በራዕይ "ወደ ወላጆችህ ተመለስ" እያለ ሦስት ጊዜ አናገረው::
ቅዱስ ዮሐንስ ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ቢጠይቀው "ራዕዩ ከእግዚአብሔር ነው" ብሎ ወደ ቤተሰቦቹ አሰናበተው::

ቅዱስ ዮሐንስ በላዩ ላይ የነበረችውን ልብስ በመንገድ ለነዳይ ሰጥቶ: በፈንታው ቆሻሻ ጨርቅ ለብሶ ከወላጆቹ በር ላይ ለመነ:: "እባካችሁ አስጠጉኝ" አላቸው:: ወላጆቹ በጭራሽ ሊለዩት አልቻሉም:: ነገር ግን አሳዝኗቸዋልና በበራቸው አካባቢ ትንሽ ቤት ሠሩለት::

በዚያች በዓት ውስጥ እንዳስለመደ በትጋት ለሰባት ዓመታት ተጋደለ:: በእነዚህ ዓመታት እንኳን ሌላው ሰው ወላጆቹም ቢሆኑ ፍርፋሪ ከመስጠት በቀር አይቀርቡትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ "ይሸተናል" የሚል ነበር:: በመጨረሻም መልአከ እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ "ከሰባት ቀናት በኋላ ታርፋለህ" አለው::

እናቱን ጠርቶ "አንድ ነገር ልለምንሽ" አላት:: "እሺ" አለችው:: "ከሞትኩ በኋላ በለበስኳት ጨርቅ እንድትገንዙኝ: በበዓቴ ውስጥም እንድትቀብሩኝ" አላትና የወርቅ ወንጌሉን አውጥቶ ሰጣት:: ያን ጊዜ አባቱም ደርሶ ነበርና ደነገጡ::

የወርቅ ወንጌሉን ለዩት:: ልጃቸውን ግን መለየት አልቻሉምና እያለቀሱ ስለ ልጃቸው የሚያውቀው ካለ እንዲነግራቸው ለመኑት:: እርሱም "ልጃችሁ ዮሐንስ እኔ ነኝ" አላቸው::

በዚያ ቅጽበት ወላጆቹ የሰሙትን ማመን አልቻሉም:: በፍጹም ዋይታ እየጮሁ አለቀሱ:: ለቅሷቸውን የሰሙ ሁሉ ተሰበሰቡ:: ለሰባት ቀናት እኩሉ እያለቀሰ: እኩሉ እየተባረከ በዓቱን ከበው ሰነበቱ:: በሰባተኛው ቀን መልአኩ መጥቶ በክብር ነፍሱን ተቀበለ::

እናቱ የልጇን አደራ ረስታ (እሷስ መልካም አደረግሁ ብላ ነው) ለሠርጉ ባዘጋጀችው የወርቅ ልብስ ገነዘችው:: ወዲያው ግን በጽኑ ታመመች:: አባት ግን ፈጠን ብሎ በዚያች ጨርቅ ገንዞ በበዓቱ ውስጥ ቀበረው:: ያን ጊዜ እናት ፈጥና ዳነች:: ከቅዱሱ መቃብርም ብዙ ተአምራትና ፈውስ ተደርጓል::

††† ቸሩ አምላካችን ከቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

††† ሐምሌ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ

††† "እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ: የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ: በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ:: በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ:: የመዳንንም ራስ ቁር: የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ:: እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው:: በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ:: በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ::" †††
(ኤፌ. ፮፥፲፬)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
👇👇👇👇👇👇
@mahibretsadkan
@mahibretsadkan
@mahibretsadkan
ናህዲ ማሕሙድ ሙትዋሊ ክፍል 8 በነጋታው ቢሮየ ድርስ
ናህዲ ማሕሙድ ሙትዋሊ

ክፍል 8

በነጋታው ቢሮየ ድርስ እንድትመጣ ነገርኳት።

እርሷም ያለማወላወል አደረገችው። በትዕቢት መንፈሰ አንገቴን ወደ ወንበሩ አዘን ብየ እንድትቀመጥ አመላከትኳት።

እርሷም እሺ ብላ ተቀመጠች። የምታደርገውን ሁሉ በአትኩሮት እክታተል ነበር። ቀድሞ ከማውቃቸው ሁሉ ለየት ያለች ናት።

ጠንካራ ሰብእና፣ ድፍረት፣ የደስደስ ያለው ገጽታ እና በራስ የመተማመን ችሎታ ታድሏታል።

ምንም ዓይነት ትችት ባዘንብባትም አትደናገጥም። የምፈልጋቸው ዓይነት ጠባይዐፈት ያሏት ሴት ትመስላለች።

በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጌዜ ሐፍረት ተሰማኝ። ምንም እንኳን እኔ የ45 ዓመት

ሴት እርሷ ደግሞ በሠላሳዎቹ ውስጥ ያለች ወጣት ብትሆንም ውስጤ ግን ከእርሷ እጅግ ያነሰኩ ያህል ይሰማው ነበር።

የሥራ ግንኙነታችንን ሁኔታ መላልሼ ገመገምኩት። ሳሚያ ሥራዬን ቀላል እና ቀና ለማድረግ ዘወትር ትጥራለች።

ከእኔ በላይ የእኔን የሥራ ጫና ተሸክማለች። የምትወደኝ መሆንዋን እንድገነዘብ ለማድረግ ምንጊዜም ጥረት ታደርጋለች።

እኔ ግን ይህንን ሁሉ ክብካቤና ጥንቃቄ ለእኔ ለማድረግ ለምን እንደምትፈልግ ዕንቆቅልሽ ሆኖብኛል።

ምናልባትም በት/ቤቱ ያሉ ክርስቲያኖች ሰለ እኔ ጠባይ እና ከእኔ ምን መጠበቅ እንዳለባት አስቀድመው ሳይነግሯት እንደ ልቀሩ ገምቻለሁ።

ሳሚያን ከመጥላት ይልቅ እንዴውም በየጊዜው እየወደድዃት መጣሁ።

ለየት የንግግር ችሎታ ፣ ለሰላሳ ድምፅ፣ ትኅትና እና ጥበብ በእርሷ ዘንድ አሉ።

የተረጋጋ እና ሰላማዊ የሆነ ድባብም በዓይኗ ላይ ረብቧል። እኔ ግን እነዚህ ነገሮች አንሥቼ አሰተያየት ሰጥቻት አላወቅም።

ምንም እንኳን የትምህርት ቤቱ ንግሥት እኔ መሆኔን ባውቅም እርሷ ግን በሁለመናዋ ከእኔ ላቅ ብላ ትታይ ነበር።

እኔም እያደር ሳሚያን ይበልጥ እየወደድኳት መጣሁ።

በመካከላችን መራራቅ ቀርቶ ወዳጅነት እየጠነከረ መጣደ ከውስጧ አንዳች ልዩ የሚስብ፣ የሚማርክ እና የሚቆጣጠር ነገር አላት።

እኔም ይህንን ተሰጥኦዋን ለመመርመር ወደድኩ። ለዚህ እንዲያመቸኝም የሆነ ምክንያት እያፈ ጠርኩ እርሷን ወደ ቢሮዬ እጠራት ነበር።

አንድ ቀን በጥቅምት 1997 ዓም ለብዙ ሰዓታት ሳንሰለቻች ከተጨዋወትን በኃላ <<ሳሚያ ለመሆኑ በእግዚአብሔር ታምኛለሽ?>> ስል እንደዋዛ ጠየቅኳት።

እርሷም <<አዎ፣ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለም >> ስትል መለሰችልኝ።

ጆሮዬን ማመን ነው ያቃተኝ። እጅግ በጣም ተገርሜ << ክርስቲያኖች በአንድ አምላክ ብቻ ነው እንዴ የሚያምኑት ?>>

ስል ጠየቅኳት። እርሷም መለሰ አድርጋ <<አዎን በአንድ አምላክ ነው የምናምከው >> ስትል መለሰችልኝ።

እኔም <<እኔ አንደሚገባኝ ግን ክርስቶስ እና ድንግል ማርያም የሚባሉ ተጨማሪ አማልክት አሏችሁ።>> አልኳት።

እርሷም ተመቻቸችና <<ያማ በብዙ አማልክት ማማለከ ነው።

እኛኮ በብዙ አማልክት እናም ልክም፣ የምናመልከው በአንድ አምላክ ነው።>> ቀጠል አድርጋም << ድንግል ማርያም የኢያሱ ክርስቶስ እናት እንጂ አምላክ አይደለችቻ>> ስትል ገለጠችልኝ።

አንድ ትልቅ ፒራሚድ አናቴ ላይ የተናደ ነበር የመሰለኝ።

ይቀጥላል

💚 @ortodoxmezmur21
💛 @ortodoxmezmur21
❤️ @ortodoxmezmur21
ሰላም የጥበብ ወዳጆች እና ውድ የዚህ ድንቅ የጥበብ
ሰላም የጥበብ ወዳጆች እና ውድ የዚህ ድንቅ የጥበብ ቻናል ተከታታዮች እንዴት አላችሁ እግዚአብሔር በያላችሁበት ሰላሙን ፍቅሩን ያብዛላችሁ ትንሽ ተራርቀናል መሰለኝ ካሉኝ ጥበቦች መሀከል ጸሎተ ዕለታ በተለያየ የጥበብ አይነት ልልክላችሁ እያሰብኩ ነው እና ይህ የፀሎተ ዕለታት ማለት ማንኛውም ዓይነት ጥበብ ሊሆን ይችላል ይህ ማለት ልክ እንደ ዕለት ተዕለት ጸሎታችን ዘወትር የምንደግመው የማናቋርጠው ነው እና ይሄም በብዙ አይነት አለ
ሰሞኑን በዚሁ እየጠየቃችሁኝ ስትወስዱት የነበረው በድጋም ብቻ ካለገቢር ሁሌም ዘወትር ዕለት ዕለት የተማርነውን እንዳንዘነጋ የሚደገም ነበር

አሁን በሰው ዘንድ ተወዳጅ እንድንሆን ፍቅር እንድናገኝ መልካምና ጥሩ ነገር እንዲገጥመን ያሰብነው እንዲሳካ የልቦናችንን ሀሳብ ፈቃድ የሚፈጽም ምንገዳችንን የሚጠርግ ጥበብ ልሰጣችሁ አስቢያለሁ እና ሁላችሁም ትጠቀሙበት ዘንድ እነሆ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፩ዱ አምላክ ጸሎት በእንተ ግርማ ሞገስ ወመስተሳልም ወመፈጽመ ኵሉ ሀልዮ ወሲሳየ ዕለት ዝ ውእቱ አስማቲሁ ለእግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ ዘተናገሮ በመንፈስ ቅዱስ በነገረ እብራይስጥ ኦ ድንግል ጥብሪዳ ኤርጋና ባርጆም በረርጆም በረጆሎማ ሶልያና ሳይዳ በርደሊስ በርደጊስ በርደሊስ ማርያም ሚርሀሊም ከመ ተሀበኒ ግርማ ወሞገሰ ሰላመ ወፍቅረ አስተሳልመኒ ለኩሎሙሕዝበ ክርስቲያን ውሉደ ጥምቀት ለዓለመ ዓለም አሜን
ገቢር፦፯ ጊዜ ደግመህ/ሽ/ ወደ ዕለት ተዕለት ተግባርህ/ሽ/ ሂድ/ሽ/ ግርማ ሞገስ ያላብስሀል/ሻል/ ከሰው ያፋቅርሀል/ሻል/


የጥበብ ቻናላችንን ለመቀላቀል👇👇👇👇
@orthodo221 💚
@orthodo221 💛
@orthodo221 ❤️
ፕሮሞሽን ቻናል ለመቀላቀል👇👇
@mahibretsadkan
ኦርቶዶክሳዊው ንባብ በዓለማችን ላይ የሚታተሙ ብዙ የታሪክ መጻሕፍት
+++ ኦርቶዶክሳዊው ንባብ +++

በዓለማችን ላይ የሚታተሙ ብዙ የታሪክ መጻሕፍት አሉ፡፡ እነዚህ የታሪክ መጻሕፍት ‹‹እንዲህ ነበረ፣ እንዲህ ሆነ፣ እንዲህ ተፈጸመ›› እያሉ ያለፈውን ዘመን አሁን ላይ ሆኖ ለሚያነብ ሰው በትረካ መልክ የሚያስቃኙ ናቸው፡፡ አንባቢው በመጽሐፉ ከእርሱ በፊት ቀድመው ስለሆኑ ነገሮች መረጃዎችን ያገኝ እንደ ሆነ እንጂ ራሱን የታሪኩ አንድ አካል የሚያደርግበት እድል የለውም፡፡ የታጠሩበት የዘመን አጥር ጥብቅ ነው፡፡ በቅጥሩ ያሉ አይወጡበትም፡፡ የሌሉ እና ያልነበሩትም አይገቡበትም፡፡

በክርስቲያኖች እጅ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከእነዚህ የታሪክ መጻሕፍት የተለየ ነው፡፡ በውስጡ የሚገኙት ታሪኮች በአንድ ወቅት የተፈጸሙ ቢሆኑም በዛሬ ዘመን ያሉ አንባብያንን ወደ ታሪኩ መጋበዝ የሚያስችል የተከፈተ በር አላቸው፡፡ የትላንቱን ከአሁን ጋር የሚያያይዙበት የተቀደሰ ሰዓት (Sacred time) አላቸው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ አንድ ጊዜ ስለ ፈጸመው የማዳን ሥራ በሚናገርበት የዕብራውያን መልእክቱ ላይ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና›› ሲል የሚመሰክረው፡፡(ዕብ 4፡12) ቤተ ክርስቲያናችንም ሕያው በሆነው በእለተ አርቡ የቀራንዮ መከራ እለት እለት በቅዳሴ ከልጆቿ ምእመናን ጋር ትመላለስበታለች፡፡ ጌታዋን እግር በእግር እየተከተለች መከራውን ትቆጥራለች፣ በስቅለቱ ታዝናለች፡፡ በመስቀሉ ያፈሰሰውን ደም በጽዋ ቀድታ፣ የቆረሰውን ሥጋ በጻሕል ተቀብላ ለልጆቿ ለምእመናን ትሰጣለች፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ባሕል ይህ ነው፡፡ አንባቢው ቃሉን ከላይ ብቻ የሚያነብ ሳይሆን በተዘክሮ ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ራሱን የታሪኩ ተካፋይ ያደርጋል፡፡

እግዚአብሔር ከእመቤታችን በተወለደ ጊዜ በጨርቅ መጠቅለሉን፣ በተናቀው ቦታ በበረት ማደሩን አይቶ ትሕትናውን ያደንቃል፡፡ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን ይዘው ወደ ጌታ እንደ መጡ ባነበበ ጊዜ፣ እርሱም ከእነርሱ ጋር ሆኖ የንጽሕናውን እጅ መንሻ ለአምላኩ ሰግዶ ያቀርባል፡፡ ከእረኞቹም ጋር መወለዱን ይናገራል፡፡ በልቡ ደስታም እያሸበሸበ አብሯቸው ይዘምራል፡፡ ወደ ቤተ መቅደስም እንዳገቡት ባነበበ ጊዜ ከአረጋዊው ስምዖን ጋር በተዘክሮ ጌታን ይታቀፈዋል፡፡ ወደ ግብጽም ሲሰደድ ጌታን፣ እናቱና ዮሴፍን ተከትሎ ይሰደዳል፡፡ በእናቱም እቅፍ ያለውን የሕፃኑን ጌታ የተወደደ መዓዛ ያሸታል፡፡ ክፉው ሄሮድስም ሲሞት አብሯቸው ወደ ገሊላ ይመለሳል፡፡

ጌታ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ መቅደስ ገብቶ መምህራንን በጠየቀ ጊዜ አጠያየቁን ያደንቃል፡፡ ወደ ዮርዳኖስ ባሕር ለጥምቀት ሲወርድ አብሮት ይወርዳል፡፡ ከሰማይ የወጣውን የአብን ድምጽ ሰምቶ፣ በርግብ ምሳሌ የወረደውን መንፈስ ቅዱስ አይቶ በሦስትነቱ ያምናል፤ በባሕር መካከል ለቆመው አካላዊ ቃልም ይሰግዳል፡፡ በቆሮንቶስም በረሃ ከጌታው ጋር አብሮ ይጾማል፡፡ በጌታ በቃና ዘገሊላ ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን ሊለውጥ ጋኖቹን በውኃ ሙሉ ባለ ጊዜ፣ ከአገልጋዮቹ ጋር ሆኖ ውኃን ይሞላል፡፡ የተለወጠውንም ወይን ቀድቶ ለአሳዳሪ በመስጠት በጌታው ተአምር ደስ ይሰኛል፡፡ እንዲህ አድርጎ ቅዱሱን መጽሐፍ እያነበበ በተዘክሮ ጌታው ከዋለበት ውሎ ካደረበት ያድራል፡፡

በዲያቆን አቤል ካሳሁን

@ortodoxmezmur21
@mahibretsadkan
@orthodo221
ሰላም እንደምን አላችሁ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ካላችሁ ለቻናላችሁ ባነር
ሰላም እንደምን አላችሁ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ካላችሁ ለቻናላችሁ ባነር ወይም ሎጎ በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራለን። ወይም በፕሮሞሽን እንሰራላችኋለን ቀለል ያለ የቻናል ሎጎ ማሰራት የምትፈልጉ መጀመሪያ ለምትመጡ አሰሪዎች በ75 ብር እንሰራላችኋለን።
@habmisget አናግሩን

3649838

Каналов

204424659

Сообщений